ሱቅዎ በእጅዎ መዳፍ።

ዕቃዎን፣ ሽያጭዎን፣ ዱቤዎንና ትርፍዎን በአንድ ስልክ ይቆጣጠሩ። ደንበኛ የቴሌብር ወይም የሲቢኢ ክፍያ ሲያሳይዎ ደግሞ፣ ዕቃውን ከማስረከብዎ በፊት ብሩ በእርግጥ መግባቱን ያረጋግጥልዎታል።

ቴሌብር ሲቢኢ ብር
የሚረጋገጠው በባንኩ የራሱ የደረሰኝ ገጽ ላይ ነው
ክፍያ ፈታሽ ሽያጭ480.00 ብር
  • እውነተኛ ደረሰኝ ነውበባንኩ የራሱ ገጽ ላይ ተገኝቷል
  • የዛሬ ክፍያ ነው28/09/2026, 12:48
  • ብሩ ሙሉ ነው480.00 ብር ገብቷል
  • የገባው ወደ እርስዎ ሂሳብ ነውየሺመቤት ዘነበ፣ ሲቢኢ
  • አዲስ ደረሰኝ ነውከዚህ በፊት ቀርቦ አያውቅም
ብሩ ገብቷል አይቀበሉ!
ይሞክሩት፦

ስክሪንሾት ብር አይደለም።

  1. ደንበኛው የቴሌብር ስክሪንሾት ያሳይዎታል።

  2. ልክ ይመስላል። ዕቃውን ያስረክባሉ።

  3. ብሩ ግን አልገባም።

  4. ማታ ሂሳብ ሲያዩ ሰውየው ሄዷል።

ክፍያ ፈታሽ ደንበኛው ቆጣሪው ላይ እያለ፣ ደረሰኙን ከባንኩ የራሱ ገጽ ጋር በሰከንዶች ያመሳክራል። የውሸት ስክሪንሾት ይህን ፈተና ማለፍ አይችልም።

«ሸጥኩ» ማለት «አተረፍኩ» ማለት አይደለም።

ብዙ ሱቆች ሽያጫቸውን ያውቃሉ፤ ትርፋቸውን ግን በወር መጨረሻ በግምት ነው የሚያውቁት። ካይሮስመዝገብ እያንዳንዱን እንቅስቃሴ ይመዘግባል፤ ሂሳቡ ራሱ እውነቱን ይነግርዎታል።

የአንድ ሚኒ ማርኬት የአንድ ወር ሂሳብ (ለምሳሌ)
ሽያጭ
500,000
የተሸጠው ዕቃ ዋጋ
−368,200
ኪራይ፣ ደመወዝና ሌሎች ወጪዎች
−58,400
በእጅዎ የቀረው ትርፍ
73,400 ብር

ቆጣሪው የሚፈልገው ሁሉ፣ በአንድ እጅ።

አንዱን ይንኩ፤ እውነተኛውን ገጽ ያያሉ።እውነተኛውን ገጽ ለማየት ወደ ጎን ያንሸራቱ።

በሰከንዶች ይሽጡ
የቴሌግራም ቦቱ የዛሬ ሽያጭ፣ ትርፍና ዕቃ ሪፖርት በአማርኛ ሲልክ

ሱቅዎን በሙሉ ከቴሌግራም ያስተዳድሩ።

መተግበሪያውን መክፈት እንኳ አያስፈልግዎትም። የትም ቢሆኑ ሽያጭዎ፣ ትርፍዎና ዕቃዎ በየቀኑ በሚጠቀሙበት ቴሌግራም ይደርስዎታል።

  • /today
    ይጠይቁ፤ ወዲያው ይመልሳልየዛሬ ሽያጭ፣ ትርፍ፣ ዱቤና ያለዎት ዕቃ ዋጋ በሰከንዶች።
  • ሳይጠይቁ በየቀኑ ሪፖርትከሱቁ ርቀው ቢሆኑም የዕለቱ ሂሳብ በራሱ ይላክልዎታል።
  • ዕቃ ከማለቁ በፊት ያሳውቅዎታልሊያልቅ የተቃረበና ያለቀ ዕቃ ሲኖር ይነግርዎታል፤ ዝርዝሩን በአንድ ንክኪ ያያሉ።
  • ሙሉው መተግበሪያ በቴሌግራም ውስጥ«መተግበሪያ ክፈት» ሲጫኑ ከቻቱ ሳይወጡ ይሸጣሉ፣ ዕቃ ያያሉ፣ ዱቤ ይመዘግባሉ።

በሦስት እርምጃ ሥራ ይጀምሩ።

  1. ፩

    ሂሳብ ይክፈቱ

    በስልክዎ፣ በጥቂት ደቂቃዎች። ኮምፒውተር አያስፈልግም።

  2. ፪

    ዕቃዎን ያስገቡ

    በስልክዎ ካሜራ ባርኮድ ይቃኙ፤ ወይም ያለዎትን የኤክሴል ዝርዝር ያስገቡ።

  3. ፫

    መሸጥ ይጀምሩ

    የመጀመሪያውን ክፍያ በአምስት ደቂቃ ውስጥ ያረጋግጣሉ።

  • በአማርኛ የተሰራመተግበሪያው በሙሉ በአማርኛ ነው፤ እንግሊዝኛም አለው።
  • በካርቶንም በፍሬምየጅምላና የችርቻሮ ዋጋ በአንድ ዕቃ ላይ፣ በብር።
  • ቴሌብርና ሲቢኢ ብርደንበኞችዎ በእርግጥ የሚከፍሉባቸው።
  • ዱቤ እንደ ልማዳችንከመጀመሪያው አብሮ የተሰራ እንጂ ተቀጥሎ የመጣ አይደለም።

ለሱቅዎ መጠን የሚሆን ዋጋ።

በነፃ ይጀምሩ። ሱቅዎ ሲያድግ ወደሚቀጥለው ይሸጋገሩ።

ሁሉንም ዕቅዶች ለማየት ወደ ጎን ያንሸራቱ

ነፃ

0ብር በወር

ፈታሹን ለመሞከር

  • በወር 20 የክፍያ ማረጋገጫ
  • የመጀመሪያው ማረጋገጫ በ5 ደቂቃ
  • አንድ ብር የሚቀበሉበት ሂሳብ
በነፃ ይጀምሩ

ጀማሪ

500ብር በወር

አንድ ቆጣሪ ላለው አነስተኛ ሱቅ

  • ያልተገደበ የክፍያ ማረጋገጫ
  • ዕቃ፣ ሽያጭና ወጪ
  • ትርፍና መሰረታዊ ሪፖርቶች
  • የዱቤ መዝገብ
ጀማሪን ይምረጡ
ብዙ ሱቆች ይህን ይመርጣሉ

ንግድ

999ብር በወር

ብዙ ገንዘብ ተቀባይ ወይም ቅርንጫፍ ላለው

  • ጀማሪ ያለው ሁሉ
  • ብዙ ገንዘብ ተቀባዮችና ቅርንጫፎች
  • ግዢና የአቅራቢ ዕዳ
  • የእያንዳንዱ ገንዘብ ተቀባይ ሪፖርት
ማሳያ ይያዙ

ድርጅት

በስምምነት

ለትልቅና ብዙ ቅርንጫፍ ላለው ድርጅት

  • ንግድ ያለው ሁሉ
  • ያልተገደበ ቅርንጫፍና ተጠቃሚ
  • ቅድሚያ የሚሰጠው ድጋፍና ስልጠና
  • በራስዎ ስምና ከሌሎች ሲስተሞች ጋር ትስስር
ይደውሉልን

ሱቆች የሚጠይቁን።

ኮምፒውተር ያስፈልገኛል?

አያስፈልግም። አሁን ባለዎት ስማርት ስልክ ይሰራል፤ ከፈለጉ በኮምፒውተርም መጠቀም ይችላሉ።

ሠራተኞቼ እንግሊዝኛ ባይችሉስ?

ችግር የለም። መተግበሪያው በሙሉ በአማርኛ ነው፤ ገንዘብ ተቀባይዎ በራሱ ቋንቋ ይሰራበታል።

የውሸት ስክሪንሾት እንዴት ይያዛል?

ፎቶውን አያምንም። የግብይት ቁጥሩን ወስዶ በባንኩ የራሱ የደረሰኝ ገጽ ላይ ይፈልገዋል፤ ከዚያ የብሩን መጠን፣ ቀኑን፣ ተቀባዩንና ከዚህ በፊት ቀርቦ እንደሆነ ያመሳክራል።

መረጃዬ የማን ነው?

የእርስዎ ነው። በፈለጉት ጊዜ ወደ ኤክሴል አውርደው መውሰድ ይችላሉ።

ለመጀመር መክፈል አለብኝ?

የለብዎትም። ነፃው ዕቅድ በወር 20 የክፍያ ማረጋገጫ ይሰጥዎታል፤ ሲያስፈልግዎ ብቻ ያሳድጉ።

ትርፍን በግምት፣ ክፍያን በስክሪንሾት መቀበል ይብቃ።

ሱቁን በሙሉ በአንድ መተግበሪያ ያስተዳድሩ፤ በቆጣሪው ላይ ደግሞ ስክሪንሾት የማያታልለው ፈታሽ ይኑርዎት።

ስልክ
+251 94 102 5457
ኢሜይል
contact@kairosinnovate.com
መተግበሪያው
app.kairosinnovate.com
በነፃ ይጀምሩ ይደውሉ